X

By Bereket Yohannes
Wed, 16-Oct-2019, 08:38

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አንድ አምላክ ምን ይላል ❓

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አንድ አምላክ ምን ይላል?

ክፍል ፩

"እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤"

በመጽሐፍ ቅዱሳችን በብሉይ ኪዳን ላይ የተጻፉ ጥቅሶች እንመልከት፦

አንድ እግዚአብሔር፣ አንድ ቅዱስ፣ አንድ ኃያል፣ አንድ ብርቱ፣ አንድ ልዑል እያሉ

ዘዳግም ፮፥፬ " እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤"

ኢዮብ ፮፥፲ " መጽናናት በሆነልኝ ነበር፤ በማይራራ ሕመም ሐሤት ባደረግሁ ነበር፥ የቅዱሱን (Holy One) ቃል አልካድሁምና።"

መዝ. ፲፮፥፲" ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም (Holy One) መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።"

መዝ. ፸፩፥፳፪ " እኔም በበገና ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ (Holy One) አምላክ ሆይ፥ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ። "

መዝ. ፸፰፥፵፩ " ተመለሱ፥ እግዚአብሔርንም ፈተኑት፥ የእስራኤልንም ቅዱስ (Holy One) አሳዘኑት።"

መዝ. ፹፱፥፲፰ " ረድኤታችን ከእግዚአብሔር ከንጉሣችንም ከእስራኤል ቅዱስ (Holy One) ነውና።"

ኢሳ. ፩፥፬ " ኃጢአተኛ ወገንና በደል የተሞላበት ሕዝብ፥ የክፉዎች ዘር፥ ርኵሰትን የምታደርጉ ልጆች ሆይ፥ ወዮላችሁ! እግዚአብሔርን ትተዋል የእስራኤልንም ቅዱስ (Holy One) አቃልለዋል ወደ ኋላቸውም እየሄዱ ተለይተዋል። "

ኢሳይያስ ፩፥፳፬ " ስለዚህ የእስራኤል ኃያል (mighty One) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በጠላቶቼ ላይ ቍጣዬን እፈጽማለሁ፥ የሚቋቋሙኝንም እበቀላለሁ። "

ኢሳ. ፭፥፲፱ " ሥራውንም ያፋጥን፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ (Holy One) ምክር ትቅረብ፥ ትምጣ ለሚሉ ወዮላቸው! "

ኢሳ. ፭፥፳፬ " ስለዚህ የእሳት ወላፈን ቃርሚያን እንደሚበላ፥ እብቅም በነበልባል ውስጥ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል ቡቃያቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ የእስራኤልም ቅዱስ (Holy One) የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።"

ኢሳ. ፲፥፲፯ " የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት ቅዱስም (Holy One) እንደ ነበልባል ይሆናል፤ እሾሁንና ኵርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል ይበላውማል።"

ኢሳ. ፲፥፳ " በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ የእስራኤል ቅሬታ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት ከእንግዲህ ወዲህ በመቱአቸው ላይ አይደገፉም፤ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ (Holy One) በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ።"

ኢሳይያስ ፲፪፥፮ " አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፥ የእስራኤል ቅዱስ (Holy One) በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።

ኢሳ. ፲፯፥፯ " በዚያ ቀን ሰው ወደ ፈጣሪው ይመለከታል፥ ዓይኖቹም ወደ እስራኤል ቅዱስ (Holy One) ያያሉ።"

ኢሳ. ፳፱፥፲፱ " የዋሃን ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ፥ በሰዎች መካከል ያሉ ችግረኞችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ (Holy One) ያደርጋሉ።"

ኢሳ. ፳፱፥፳፫ " ነገር ግን የእጄን ሥራ ልጆቹን በመካከሉ ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብንም ቅዱስ (Holy One) ይቀድሳሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።"

ኢሳ. ፴፥፲፩ " ከጐዳናውም ዘወር በሉ፥ የእስራኤልንም ቅዱስ (Holy One) ከእኛ ዘንድ አስወግዱ ይሉአቸዋል።"

ኢሳ. ፴፥፲፪ " ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ (Holy One) እንዲህ ይላል። ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በግፍና በጠማምነት ታምናችኋልና፥ በእርሱም ተደግፋችኋልና"

ኢሳ. ፴፥፲፭ " የእስራኤል ቅዱስ (Holy One)፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። 

This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support