X

By Bereket Yohannes
Sat, 12-Oct-2019, 16:53

ኑ እንውረድ

? በማስተዋል እናምብብ

??"ኑ እንውረድ" ??

?

???


 የወረደው አንድ አምላክ ነው ወይስ ብዙ ?  ወረደ ማለትስ ምን ፊቺ አለው?


 የሚወርድስ አካል ለእግዚአብሔር ነበረው?


"ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው። እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።" (ዘፍ 11:7) 


ማለቱ አንዱ የሥላሴ አካል ሌሎቹን እያስተባበረ የሚመስላቸው አሉ። 


?መጠየቅ ያለበት ጥያቄ እግዚአብሔር ወረደ ማለት ምን ማለት ነው? 

እግዚአብሔር ሲወርድ ክብሩን የሚሸከሙ መላዕክቱ አብረውት ይወርዳሉ። እግዚአብሔር በተቆጣበት በዚህ ክስተት የክብሩ ተሸካም ኪሩቤል አብረው እንደነበሩ ማስረጃ መስጠት ይቻላል።

"ከቍጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊቱም የሚበላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥ ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ። #በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ። መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ፤ በዙሪያውም ድንኳኑ፤ በደመናት ውስጥ የጨለማ ውኃ ነበረ። በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ። እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ። ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፤ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም። (መዝ 18፡7-15)

"ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፤ #በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ተገለጥ።  በኤፍሬምና በብንያም በምናሴም፤ ኃይልህን አንሣ እኛንም ለማዳን ና።" (መዝ 80፡1)

"እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፤ #በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።" (መዝ 99:1) ተብሎ እንደተፃፈ ኪሩቤል ማለት በዛ ያለ የመላዕክት ስብስብ ከሆኑና የእግዚአብሔርን ክብር የሚሸከሙ ከሆነ #እኛ ማለቱ ለሥራ የሚጠቀምባቸውን መላዕክት ወይንም ሠራተኞቹን እንደዕቃ ሳይቆጥር አብረውት መሥራታቸውን ለመግለፅ መናገሩን ያመለክተናል እንጂ ሌሎች እግዚአብሔሮች አብረውት ነበሩ ወይም ሠሩ አልያም


 እግዚአብሔር ሥላሴ ነው ወደምል ድምዳሜ ሊወስደን አይገባም። ?ለምሳሌ አንድ ባለስልጣን?‍? የመክናውን? ሾፌር አንድ ሥራ ሰርተን እንድንመለስ ወደ አንድ ስፍራ

 "እንሂድ" በማለቱ ብቻ ሌሎች ባለስልጣናት አብረውት ሄደዋል ማለት አይቻልም።


"የጌታንም ድምፅ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ እኔም እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ።"(ኢሳ 6:8) ማለቱ ጥያቄ የፈጠረባቸው ብሎም አምላክ ሥላሴ ባይሆን እንዲህ ባላለ ነበር የሚል ሙግት የሚያቀርቡ ብዙ ናቸው። ?" ሚክያስም አለ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ ?በቀኙና በግራው ?ቆመው አየሁ። "(1ኛ ነገ 22:19)


ይህ እንግዲህ እግዚአብሔር በሥራው የሚጠቀምባቸው መላዕክቱ በተልዕኮው ተካፋይነታቸው ምክንያት በአንድ ሰው መጥፋት የሚሰማቸው እና በአንድ ሰው ንስሃ በመግባት የሚደሰቱ መሆናቸው አመላካች ነው።


 ስለዚህ "ኑ እንውረድ " በዚህም ክፍል ቢሆን ከእኩያ አማልክት ወይም ከሌሎች መለኮታዊ አባላት ጋር የሚመካከር ሳይሆን ለሚወዳቸው ቅዱሳኑ እና መላዕክቱ ሀሳቡን መግለጡን ያሳያል።

ወረደ የሚል ቃል ጥሬ-ትርጉም (literal meaning) ብንቀበለው እንኳ (አንቀበልም እንጂ) ክርስቶስ በሥጋ ከመምጣቱ በፊት ለእግዚአብሔር የሚወርድ  አካል አልነበረው አካሉ ክርስቶስ ነውና። " እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።"(ቆላ 2:17)


ሲናጠቃልል "ኑ እንውረድ" መባሉ የአማልክት ኮምቴ ወደምድር ወረዱ ለማለት አለመሆኑና ። እዚያው ምዕራፍ ትንሽ ከፍ ብለው ቢያነቡ የወረደው አንድ ?እግዚአብሔር እንደሆነ ያረጋግጣል። 

" እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።"(ዘፍ 11:5) ለየግላቸው እግዚአብሔር የሆኑ ወረዱ ሳይሆን አንዱ አምላክ እንደወረደ ያሳያል።

This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support