?????????????
✔️የማንን_እንስማ❓
የሰውን ወይስ? ክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን እንስማ❓
መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እንጂ የሰው ቃል እንዳይደለ አረጋግጦ ማመን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ “ይህን በመጀመሪያ እውቁ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልወጣምና ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልኮ ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” 2ኛ ጰጥ 1÷20-21፣ ኢሳ 34÷16
#ሰው_የሚለው፡- የኢየሱስ ወይስ የጴጥሮስን እንስማ በማለት መጽሐፍ ቅዱስን ለሁለት ከፍሎ የሰውና የእግዚአብሔር አድርጎታል፡፡
#ኢየሱስ_የሚለው_ግን፡- የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብጹዕ ነህ እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እስራለሁ የገሃም ደጆች አይችሉአትም፡፡ መንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እስጥሃለሁ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” የሚል ነው፡፡ ማቴ 16÷17-19÷ሐዋ 238
#ሰው_የሚለው፡- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር የኢየሱስና መንፈስ ቅዱስ የማዳን ስም ነውና ለጥምቀት ስንጠቀምበት ያድናል ነው፡፡
#ኢየሱስ_የሚለው_ግን፡- የእግዚአብሔር አብም ወልድም መንፈስ ቅዱስም አዳኝ ስም ኢየሱስ የተባለው ስሜ ብቻ ስለሆነ ለእግዚአብሔር አብ ክብር የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ አድርጉት ነው ማቴ 1÷20-23፣ ሉቃ 24÷47፣ ቆላ 3÷187፣ ፊል 2÷9-11፣ ሐዋ 4÷12 ዮሐ4÷12 5÷43፣ 16÷23-24፤ 17÷26፡፡
#ሰው_የሚለው፡- አብና ወልድ በሰማና በምድር ለብቻቸው በየአካላቸው ይኖሩ ስለነበረ ወልድ ወደ ሰማይ እያየ ይጸልያል ነው፡፡
#ኢየሱስ_የሚለው፡- “እኔና አብ አንድ ነን” እኔ በአብ አብም በእኔ ውስጥ በተዋህዶ እንዳለን እመኑ እመኑ ነው፡፡ ዮሐ 10÷30፤ 14÷6-10 ኢየሱስ እርግጠኛውን የሚያስተምር የማይዋሽ መምህርና ስለራሱም ከራሱ በላይ የሚያውቅ ሌላ ስለሌለ “እውነት እውነት እልሃለሁ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን ምስክራችንንም አትቀበሉትም ስለምድራዊ ነገር በነገርኳችሁ ጊዜ ካላመናችሁ ስለሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ስማይ የወጣ ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡ በማለት ራሱ እንደአብ በሰማይ ሙላት እንደወልድ በምድር በምድር መኖር የሚችል አንደነበረ አረጋግጦአልና፡፡ የአብንና የወልድን የአካል አንድነት ከወልድ ስለተማርን አካል አንድነቱን ልንክድ አንችልም ዮሐ 3÷11-13
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
This site was designed with Websites.co.in - Website Builder
We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!
Have a great day!
Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support